ኖላዊት/ቡጥቃ/Nolawit (@nolawit) 's Twitter Profile
ኖላዊት/ቡጥቃ/Nolawit

@nolawit

ኢትዮጲያዊት💚💛❤️|Farmer|Pan-Africanist|Poetry Lover|

ID: 44071331

calendar_today02-06-2009 06:10:42

189 Tweet

99 Followers

125 Following

ኖላዊት/ቡጥቃ/Nolawit (@nolawit) 's Twitter Profile Photo

ህዝቡ ያልቦካ ሊጥ፣ ሃገር ገበር ምጣድ፣ ከላይ ፍም ከታች ፍም ምን እሳቱ ቢነድ፣ ፍሙ ቢተረከክ፣ ሸክላው ለጉድ ቢግም ማገዶ ይፍጅ እንጂ፣ ይህ ትውልድ አይበስልም የዘመኑ ነገር ያደከመ ለታ እንዲህ ብለን ነበር!!!

ኖላዊት/ቡጥቃ/Nolawit (@nolawit) 's Twitter Profile Photo

ህዝብሽ በአብዛኛው ሆነና የሚያድር አውርቶ ህብረት የሚበትን ሊያውም እንቶ ፈንቶ እኔ አይቶ ዝም ብጠላም ብጠየፍ አምርሬ ልውጣ ልውጣ እያለ የሚተናነቀኝ ስንት እውነት ቀብሬ ስለጠላሽ ወሬ ዝምምምም ጭጭ አልኩልሽ የኔ ዝም ማለት ይጥቀምሽ ሃገሬ

ኖላዊት/ቡጥቃ/Nolawit (@nolawit) 's Twitter Profile Photo

አድዋ እናት አባቶችህ ተዋድቀው ከፍ አድርገው የሠቀሉልህ የነፃነትህ ምልክት፣ የጥቁር ዘር በሙሉ የሚኮራበት አንፀባራቂ ድል ነው!! በደም የተገዛ፣ በአጥንት የተከፈለ፣ የትውልድህ ሁሉ ውርስ ነው! አድዋ የእኔ፣ የአንቺ፣ የአንተ ነው!

ኖላዊት/ቡጥቃ/Nolawit (@nolawit) 's Twitter Profile Photo

እኔ - ልጅህን ማን አልካት? ጓደኛ ፩ - ስናፍቅሽ ጓደኛ ፪ እና ፫ ከሳቅ ጋር - አውቀህ፣ አታደርገውም! እኔ - ጎሽ እንኳን ትርጉሙ ለነፍስህ የሚቀርብ ሃገርኛ ስም አወጣህላት ሃገርኛ ስም የፋራ ተደርጎ የሚቆጠረው ነገር እራሱ የፋራ የሚሆነው መቼ ነው?

ኖላዊት/ቡጥቃ/Nolawit (@nolawit) 's Twitter Profile Photo

Why??? ውይ ሠላምታ እኮ ከሃገራችን ከምናቆራኛቸው ኢትዮጲያዊ መልክ ያለው አንዱ ነገራችን ነው!! thereporterethiopia.com/article/iconic…

ኖላዊት/ቡጥቃ/Nolawit (@nolawit) 's Twitter Profile Photo

Arabica coffee መገኛይቱን፣ ህዝቧም ኢኮኖሚዋም በቡና የሚነቃቃላትን ሃገር.... እነዚን 13% ሠዎች በያሉበት ከቦ ማናገር ነው!!

ኖላዊት/ቡጥቃ/Nolawit (@nolawit) 's Twitter Profile Photo

ቅሉ ለአመታት በተከፈተበት መጠነ ሠፊ ዘመቻ፣ ከአባቶቻችን ከፍታ ሸርተት ብሎ ከኢትዮጲያዊነታችን ወረድ ብሎ የታየ ቢመስልም እንኳን... ፈተናውን ተጋፍጦ ያባቶቹን ህልም እውን ሊያደርግ በብዙ መስዋትነት ግድቡን እየገነባ ያለው "የኔ ትውልድ ነው"!!

ኖላዊት/ቡጥቃ/Nolawit (@nolawit) 's Twitter Profile Photo

አናሳዝንም ወይ እንዲል ቴዲ አፍሮ!! ከልጅነት እስከ እውቀት የኖርንባት ይህች ከነምኗ ከነምናምኗ የምንወዋዳትና የኔ የምንላት ውብ ሃገር፣ የእርስ በርስ ጦርነቷ ቆሞ ከስጋት ነፃ በሆነ ጭንቅላት ስለእድገቷ የምናስብበት ቀን ይመጣ ይሆን? አረረረረ

ኖላዊት/ቡጥቃ/Nolawit (@nolawit) 's Twitter Profile Photo

እሷ - ከመሸ ደወልኩ፣ አልተኛህም አይደል እሱ - እንቅልፍ ድህነት ነው፣ በየትኛው ባለፀጋነቴ ነው በዚህ ሠአት የምተኛው!! ህዝባችን በችግሩ ላይ ያላግጥበታል ነው የሚባለው!!

ኖላዊት/ቡጥቃ/Nolawit (@nolawit) 's Twitter Profile Photo

ጓዴ ትላንት ለነዳጅ 4 ሠአት ተሰልፌ ቀዳሁ አለች!! ነዳጅ ጣቢያ ሠራተኞች፣ ቴሌ ብር መተግበሪያ እና እኛ ተጠቃሚዎች ተግባብተን የነዳጅ ወረፋው እስኪቀንስ፣ ባለን ግማሽ ታንከር ነዳጅ ተብቃቅተን ይሄንን ሠልፍ እንዴት መሸወድ እንደምንችል ጠቁሙና!!