Ethiopia Insider(@ethiopiainsider) 's Twitter Profileg
Ethiopia Insider

@ethiopiainsider

Latest news, updates, insights, analysis, features, photos and videos from Ethiopia
Facebook - https://t.co/PyeNELecBQ

ID:1166455374863622153

linkhttp://www.ethiopiainsider.com calendar_today27-08-2019 21:00:47

2,9K Tweets

30,8K Followers

0 Following

Ethiopia Insider(@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

ቪዲዮ (2)፦ “ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ ያነሷቸው 1,035 አካባቢ የሚሆኑ ሰዎች፤ ከዚህ ውስጥ አንድም ሰው ቤት ሳይሰጠው፣ ተነስቶ ሌላ ቦታ የገባ ሰው የለም። የመንግስት ቤት ተከራይ፣ የቀበሌ፣ የኪራይ ቤቶች፣ የቤተክህነት ጭምር ማለት ነው” - አዳነች አቤቤ

account_circle
Ethiopia Insider(@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

ቪዲዮ፦ በዛሬው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ የምክር ቤቱ አባል የሆኑት ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ፤ ከኮሪደር ልማት ተነሺዎች መካከል 1,135 ሰዎች ምትክ ቤት ወይም ቦታ እስካሁን አለማግኘታቸውን በማንሳት ጥያቄ አቅርበዋል።

account_circle
Ethiopia Insider(@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

ቪዲዮ፦ በአዲስ አበባ ከተማ ከተጀመረ 1 ወር ከ15 ቀናት ባስቆጠረው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት፤ 5,135 ቤቶች እንደተነሱ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ። ከልማት ተነሺዎች 20 በመቶው ካሳ አሊያም ምትክ ቦታ፣ ቤት ወይም መስሪያ ቦታ እስካሁንም አላገኙም።

account_circle
Ethiopia Insider(@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

የስፖርት ውርርድን የተመለከቱ መመሪያዎች እና ደንቦች “ጥናትን መሰረት አድርገው ሊታገዱ እንደሚገባ” የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር አሳሰበ። በስፖርት ውርርድ ምክንያት “ብዙ ቤተሰብ እየፈረሰ” መሆኑንም ገልጿል።

👉ethiopiainsider.com/2024/13008/

account_circle
Ethiopia Insider(@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

“ህግን ተላልፈው ተገኝተዋል” የተባሉ 55 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው። ከድርጅቶቹ ውስጥ አምስቱ የተሰጣቸው “ጥብቅ የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ” መሆኑን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አስታውቋል።

👉ethiopiainsider.com/2024/13005/

“ህግን ተላልፈው ተገኝተዋል” የተባሉ 55 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው። ከድርጅቶቹ ውስጥ አምስቱ የተሰጣቸው “ጥብቅ የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ” መሆኑን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አስታውቋል። 👉ethiopiainsider.com/2024/13005/
account_circle
Ethiopia Insider(@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፤ በሀገራዊ ምክክር ላይ “አጀንዳ ሊሆኑ ይገባሉ” የሚሏቸውን ጉዳዮች እንዲያዘጋጁ  ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በደብዳቤ ጥሪ አቀረበ።

🔵 ዝርዝሩን ለማንበብ👉 ethiopiainsider.com/2024/13001/

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፤ በሀገራዊ ምክክር ላይ “አጀንዳ ሊሆኑ ይገባሉ” የሚሏቸውን ጉዳዮች እንዲያዘጋጁ  ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በደብዳቤ ጥሪ አቀረበ። 🔵 ዝርዝሩን ለማንበብ👉 ethiopiainsider.com/2024/13001/ #Ethiopia #NationalDialogue
account_circle
Ethiopia Insider(@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

ባለፈው ሐሙስ ምሽት በሰሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ የተከሰተውን የእሳት ቃጠሎ በማስነሳት የተጠረጠሩ 3 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሰሜን ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ቢምረው ካሳ ለEthiopia Insider ተናገሩ።

👉ethiopiainsider.com/2024/12992/

ባለፈው ሐሙስ ምሽት በሰሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ የተከሰተውን የእሳት ቃጠሎ በማስነሳት የተጠረጠሩ 3 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሰሜን ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ቢምረው ካሳ ለ@ethiopiainsider ተናገሩ። 👉ethiopiainsider.com/2024/12992/
account_circle
Ethiopia Insider(@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

የቡድን 7 ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች ይታያሉ ያሏቸው “የማያቋርጡ እና ኃይለኛ ውጥረቶች” እንደሚያሳስቧቸው ገለጹ። ሚኒስትሮቹ የሀገሪቱ “ብርቱ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ” እንዳሰጋቸውም አስታውቀዋል።
👉ethiopiainsider.com/2024/12978/

የቡድን 7 ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች ይታያሉ ያሏቸው “የማያቋርጡ እና ኃይለኛ ውጥረቶች” እንደሚያሳስቧቸው ገለጹ። ሚኒስትሮቹ የሀገሪቱ “ብርቱ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ” እንዳሰጋቸውም አስታውቀዋል። 👉ethiopiainsider.com/2024/12978/
account_circle
Ethiopia Insider(@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

የፌደራል መንግስት የህወሓት ታጣቂዎችን በአስቸኳይ ትጥቅ እንዲያስፈታ ኢዜማ ጠየቀ። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በዜጎች ላይ ለሚደርሰው ጉዳት፤ የፌደራል መንግስት “ሙሉ ኃላፊነቱን የሚወስድ ይሆናል” ሲል ፓርቲው አሳስቧል።

* ዝርዝሩ፦ ethiopiainsider.com/2024/12973/

የፌደራል መንግስት የህወሓት ታጣቂዎችን በአስቸኳይ ትጥቅ እንዲያስፈታ ኢዜማ ጠየቀ። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በዜጎች ላይ ለሚደርሰው ጉዳት፤ የፌደራል መንግስት “ሙሉ ኃላፊነቱን የሚወስድ ይሆናል” ሲል ፓርቲው አሳስቧል። * ዝርዝሩ፦ ethiopiainsider.com/2024/12973/
account_circle
Ethiopia Insider(@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

በአዲስ አበባ ተቋርጦ የነበረው የመታወቂያ መስጠት እና እድሳት አገልግሎት በቀጣዩ ሳምንት እንደሚጀመር ተገለጸ።አገልግሎቱ የተቋረጠው በከተማይቱ የኮሪደር ልማት ሲካሄድ “በቴሌኮም ኬብሎች ላይ ጉዳት በመድረሱ ነው” ተብሏል።
👉ethiopiainsider.com/2024/12965/

በአዲስ አበባ ተቋርጦ የነበረው የመታወቂያ መስጠት እና እድሳት አገልግሎት በቀጣዩ ሳምንት እንደሚጀመር ተገለጸ።አገልግሎቱ የተቋረጠው በከተማይቱ የኮሪደር ልማት ሲካሄድ “በቴሌኮም ኬብሎች ላይ ጉዳት በመድረሱ ነው” ተብሏል። 👉ethiopiainsider.com/2024/12965/
account_circle
Ethiopia Insider(@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

ከአላማጣ እና ከሌሎች የራያ አካባቢዎች የተፈናቀሉ በሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች፤ ከቆቦ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ የኢንዱስትሪ መንደር በጊዜያዊነት እንዲጠለሉ መደረጋቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ለEthiopia Insider ተናገሩ።

👉ethiopiainsider.com/2024/12962/

ከአላማጣ እና ከሌሎች የራያ አካባቢዎች የተፈናቀሉ በሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች፤ ከቆቦ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ የኢንዱስትሪ መንደር በጊዜያዊነት እንዲጠለሉ መደረጋቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ለ@ethiopiainsider ተናገሩ። 👉ethiopiainsider.com/2024/12962/
account_circle
Ethiopia Insider(@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

ለኢትዮጵያ ሰብአዊ እርዳታ የሚውል ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ በለጋሾች ቃል ተገባ። ለጋሾቹ ይህን ቃል የገቡት፤ ዛሬ ማክሰኞ ሚያዝያ 8፤ 2016 በጄኔቫ በተካሄደ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ላይ ነው።

* ለዝርዝሩ፦ ethiopiainsider.com/2024/12957/

ለኢትዮጵያ ሰብአዊ እርዳታ የሚውል ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ በለጋሾች ቃል ተገባ። ለጋሾቹ ይህን ቃል የገቡት፤ ዛሬ ማክሰኞ ሚያዝያ 8፤ 2016 በጄኔቫ በተካሄደ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ላይ ነው። #Ethiopia * ለዝርዝሩ፦ ethiopiainsider.com/2024/12957/
account_circle
Ethiopia Insider(@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

ምስላዊ መረጃ፦ በቀጣዩ የፈረንጆቹ 2025 ዓመት፤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 6.5 በመቶ ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ IMF ዛሬ ይፋ አደረገ። ይህ የድርጅቱ ትንበያ፤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በሚቀጥለው ዓመት አነስተኛ መነቃቃት እንደሚታይበት የሚጠቁም ነው።

ምስላዊ መረጃ፦ በቀጣዩ የፈረንጆቹ 2025 ዓመት፤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 6.5 በመቶ ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ IMF ዛሬ ይፋ አደረገ። ይህ የድርጅቱ ትንበያ፤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በሚቀጥለው ዓመት አነስተኛ መነቃቃት እንደሚታይበት የሚጠቁም ነው። #Ethiopia
account_circle
Ethiopia Insider(@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

በአማራ ክልል ባቲ ወረዳ ስር ባሉ አካባቢዎች የአተት ወረረሽኝ በመከሰቱ፤ ዘወትር ሰኞ በባቲ ከተማ የሚውለው ገበያ በዛሬው ዕለት ዝግ ሆኖ እንዲውል ተደረገ። በወረዳው በ1 ሳምንት ብቻ 76 ሰዎች በወረርሽኙ ተጠቅተዋል ተብሏል።

👉ethiopiainsider.com/2024/12947/

በአማራ ክልል ባቲ ወረዳ ስር ባሉ አካባቢዎች የአተት ወረረሽኝ በመከሰቱ፤ ዘወትር ሰኞ በባቲ ከተማ የሚውለው ገበያ በዛሬው ዕለት ዝግ ሆኖ እንዲውል ተደረገ። በወረዳው በ1 ሳምንት ብቻ 76 ሰዎች በወረርሽኙ ተጠቅተዋል ተብሏል። 👉ethiopiainsider.com/2024/12947/
account_circle
Ethiopia Insider(@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

ስራቸውን በለቀቁ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኮሚሽነር ምትክ አዲስ ኃላፊ ሊሾም ነው። ለተተኪ ኮሚሽነርነት ዕጩ የሚሆኑ ግለሰቦች ጥቆማ፤ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እንደሚካሄድ ተገልጿል።

* ለዝርዝሩ፦ ethiopiainsider.com/2024/12942/

ስራቸውን በለቀቁ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኮሚሽነር ምትክ አዲስ ኃላፊ ሊሾም ነው። ለተተኪ ኮሚሽነርነት ዕጩ የሚሆኑ ግለሰቦች ጥቆማ፤ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እንደሚካሄድ ተገልጿል። * ለዝርዝሩ፦ ethiopiainsider.com/2024/12942/
account_circle
Ethiopia Insider(@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

በትግራይ ክልል በተካሄደው ጦርነት ወቅት፤ ወደ ኤርትራ ተወስደው ታስረው ከነበሩ የክልሉ ተወላጆች ውስጥ 46ቱ በዛሬው ዕለት ተለቀቁ። እስረኞቹ ዛሬ አርብ ሚያዝያ 4 ጠዋት ሸራሮ መግባታቸውን የከተማይቱ ከንቲባ ተናግረዋል።

👉ethiopiainsider.com/2024/12937/

በትግራይ ክልል በተካሄደው ጦርነት ወቅት፤ ወደ ኤርትራ ተወስደው ታስረው ከነበሩ የክልሉ ተወላጆች ውስጥ 46ቱ በዛሬው ዕለት ተለቀቁ። እስረኞቹ ዛሬ አርብ ሚያዝያ 4 ጠዋት ሸራሮ መግባታቸውን የከተማይቱ ከንቲባ ተናግረዋል። 👉ethiopiainsider.com/2024/12937/
account_circle
Ethiopia Insider(@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

ኦነግ በፖለቲካ ኦፊሰሩ በቴ ኡርጌሳ ላይ የተፈጸመውን ግድያ በአፋጣኝ እንዲመረምሩ ለሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ጥያቄ አቀረበ። አቶ በቴ በመቂ ከተማ የተገደሉት በተተኮሰባቸው ጥይት መሆኑን ኦነግ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ገልጿል።

👉ethiopiainsider.com/2024/12934/

ኦነግ በፖለቲካ ኦፊሰሩ በቴ ኡርጌሳ ላይ የተፈጸመውን ግድያ በአፋጣኝ እንዲመረምሩ ለሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ጥያቄ አቀረበ። አቶ በቴ በመቂ ከተማ የተገደሉት በተተኮሰባቸው ጥይት መሆኑን ኦነግ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ገልጿል። 👉ethiopiainsider.com/2024/12934/
account_circle
Ethiopia Insider(@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ ትላንት ማክሰኞ ሚያዝያ 1፤ 2016 ምሽት መገደላቸውን ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጹ። አቶ በቴ የተገደሉት በትውልድ ቦታቸው መቂ ከተማ እንደሆነ ምንጮች ተናግረዋል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ ትላንት ማክሰኞ ሚያዝያ 1፤ 2016 ምሽት መገደላቸውን ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጹ። አቶ በቴ የተገደሉት በትውልድ ቦታቸው መቂ ከተማ እንደሆነ ምንጮች ተናግረዋል። #Ethiopia
account_circle
Ethiopia Insider(@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

አራት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ በፓርቲ አመራሮች እና አባላት ላይ የሚፈጸሙ “እስሮች እና ማዋከቦች” እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ። አሁን በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች “በአስቸኳይ” እንዲፈቱም ጠይቀዋል።

ዝርዝሩ፦ ethiopiainsider.com/2024/12912/

አራት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ በፓርቲ አመራሮች እና አባላት ላይ የሚፈጸሙ “እስሮች እና ማዋከቦች” እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ። አሁን በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች “በአስቸኳይ” እንዲፈቱም ጠይቀዋል። ዝርዝሩ፦ ethiopiainsider.com/2024/12912/
account_circle
Ethiopia Insider(@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

በኢትዮጵያ ካሉ 1,300 ወረዳዎች ውስጥ በ850ዎቹ የምክክር አጀንዳዎች የሚለዩ ተወካዮች ምርጫ መጠናቀቁን ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ አጀንዳ የማሰባሰብ ስራውን “ባጠሩ ሳምንታት” ውስጥ እንደሚጀምርም ገልጿል።

👉ethiopiainsider.com/2024/12906/

በኢትዮጵያ ካሉ 1,300 ወረዳዎች ውስጥ በ850ዎቹ የምክክር አጀንዳዎች የሚለዩ ተወካዮች ምርጫ መጠናቀቁን ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ አጀንዳ የማሰባሰብ ስራውን “ባጠሩ ሳምንታት” ውስጥ እንደሚጀምርም ገልጿል። 👉ethiopiainsider.com/2024/12906/
account_circle